የኤጀንሲው ሃላፊ መልዕክት

የኤጀንሲዉ ስራ አስኪያጅ መልዕክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስከያጅ
ኢ/ር ካሳዬ ተክሌ ስራ
የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ በተሰጠዉ ስልጣንና ተግባር መሰረት በክልሉ የመስኖ አለኝታ ጥናት ያካሂዳል፣የመስኖ ልማትና ድሬኔጅ ስራዎች ጥናትና ዲዛይን እና የግንባታ ክትትልና ኮንትራት አስተዳደር ስራዎች ያከናዉናል ፡፡ የመስኖ ተቋማት አስተዳደር ስርአቱን ይዘረጋል፣ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡ .
በመሆኑም በ2017 በጀት አመት እንደየአካባቢዉ እምቅ የዉሀና የመሬት ሀብት የተለያዩ አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የወንዝ ጠለፋ ፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ የመስኖ ግድብ ጥናት፣የከርሰ ምድር መስኖ ቁፋሮ፣ የሶላር ፓምፕ ተከላ ጥናት እና ጥገና የሚያስፈልጋቸዉን የመስኖ ተቋማት በመለየት የመልሶ ግንባታና ጥገና ጥናት ስራዎች ለማካሄድ ታቅዶ በእቅዱ መሰረት ተከናዉኗል፡፡
በግንባታ ረገድ የነባር የመስኖ ፕሮጀክቶ ግንባታ እና መልሶ ግንባታ ለማጠናቀቅ በታቀደዉ መሰረት የሁሉም ነባር መስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቋል፡፡ ከመስኖ ተቋማት አስተዳደር አኳያ የመስኖ ተቋማት በሙሉ አቅም አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸዉ ችግሩን በመረዳት በዘለቄታዊነት ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ የመስኖ ተቋማት ቆጠራ እንዲደረግ በማድረግ በየተቋማቱ ላይ ያሉ ችግሮች ተለይተዉ የመፍትሄ አቅጣጫ የተቀመጠ በመሆኑ ከባለድርሻ አካለት ጋር ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ለቀጣይ የበጋ መስኖ ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ የመስኖ ዉሀን በፍትሀዊነት ለመጠቀም የሚመለከታቸዉ አካላት በተስማሙበት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል፣የክትትልና ድጋፍ ስራዉ በአግባቡ እንዲመራ ይደረጋል፡፡
በ2018 በጀት አመት አዳዲስ የጥናት፣ የግንባታና የመልሶ ግንባታ ስራዎች የሚጀመሩ ሲሆን ከተቋማት አስተዳደር አንጻር ለዞን፣ለልዩ ወረዳ፣ለወረዳ ባለሙያዎችና ለዉሀ ኮሚቴዎች ስልጠና በመስጠት ጠንካራ ማህበር እንዲኖር በማድረግ ተጠቃሚዎች ተቋሙን በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩና ከመስኖ ልማቱ የሚገኘዉ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግና አርሶ አደሩ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ይሰራል፣ የመልካም አስተዳደርና የለዉጥ ስራዎች ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ሲሆን ለሁሉም ተግባራት በቂ ትኩረት ተሠጥቶ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 