Skip to main content

አሀዳዊ ዋሽ (OWNP)

አሀዳዊ የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም በሀገራችን  እ.እ.አ ከ2013 ጀምሮ በሁለት የተለያዩ ምዕራፎች እየተተገበረ የሚገኝ ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በሀገሪቱ በተመረጡ ገጠር እና ከተማ አካባቢ ላይ  በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣በጤናና በትምህርት ተቋማት ላይ በሳኒቴሽን ዙሪያ  ሰፊ ማዕለ ንዋይ በማፍሰስ መንግስት በ2ኛው በትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ያስቀመጣቸውን ግቦችን በማስካት ረገድ ጉልህ ድርሻ ያለው ፕሮግራም ሲሆን የበጀት ምንጩም ዓለም ባንክ፣ ዩኒሴፍ የፊላንድ መንግስት፣ ሳውዲ አረቢያ፣ኮሪያ እና የኢትዮጲያን መንግስት የበጀት ድጋፍ  ጨምሮ በጋራ በአምስት ክፍሎች ተከፋፍሎ ማለትም የገጠር ዋሽ፣የከተማ ዋሽ፣ የተቋማት ዋሽ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጸዕኖ የሚቋቋም ዋሽ  እና የአቅም ግንባታና የፕሮግራም አስተዳደር ዋሽ  በመባል የሚተገበር ከመሆኑም በተጨማሪ አራት መርሆች የሚከተል ነው፡፡ እነሱም ቅንጅታዊ አሰራር፣ የመንግስት የፖሊሲ አቅጣጫ፣አንድ በጀት፣አንድ ዕቅድ እና አንድ ሪፖርት እንዲሁም ለሌሎች ተመሳሳይ ስራ ለሚሰሩ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ዕውቅና በመስጠት መርህ የተገነባ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የፕሮግራሙ ፌዝ-2 ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ 100,520 ለሚሆኑ የክልላችን የገጠር ማህበረሰብን የተለያዩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታና የተለያዩ የጥገናና ማስፋፊያ  ስራዎችን በመስራት የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡  

IMAGE
1.	OWNP-CWA-II Profile in CER Water Sector
2.	Activities planned in the program