የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳኒቴሽን ዘርፍ በስሩ አቅፎ ከያዛቸው ዳይሬክቶሬቶች መካከል የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ክልሉ በአዲስ ከተደራጀ ጊዜ ጀምሮ በመጠጥ ውሃ ተቋማት ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በተለያየ መንገድ እየፈታ ማህበረሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡
የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በክልሉ ከሚገኙ ሰባት ዞኖችና ሶስት ልዩ ወረዳዎች የተለያዩ የጥገና ጥያቄዎችን ተቀብሎ ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው በአስቸኳይ በመላክ መጠገን ያለባቸው ተቋማት ተጠግነው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም በማድረግ ከፍተኛ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የውሃ አቅርቦት ስርዓቱ ቀጣይነት ያለው እንዲሁም አስተማማኝ የውሃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ መደበኛ ስራዎችንና ጥገናዎችን ጨምሮ የውሃ አቅርቦት ስርዓት እንዲሰራ የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ተግባራት ያካትታል፡፡
በዳይሬክቶሬቱ የሚከወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የተጠናቀቁ የግንባታ መረጃ ያደራጃል፣ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያስተላልፋል፣
የአካባቢ ሙያተኞችን ማደራጀት፣ማሰልጠንና ማብቃት
የገጠር/ከተማ የተቋማት የውሃ ተቋማት የሚያስተዳድሩ አካላት ማደራጀት፣ማሰልጠን፣ማብቃት
ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
የኤሌክትሪክ ብልሽት የገጠማቸውን እንደ ኤልክሮድ፤ሬጉሌተር፤ትራንስፎርመር ፤ኮንታክተር ያሉ መለዋወጫዎችን መጠገን መቀየር
ለኤልክትሮ መካኒካል መሣሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት
የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ኦልተርኔተር ስዊች እና ኮንትሮል ፓናል ጥገና ማከናወን
የተቋማት የጥገና መረጃዎች በየወቅቱ መዝግቦ ማስቀመጥ
መለዋወጫዎች እና ኤሌክትሮ መካኒካል መሣሪያዎች ግዥ መፈጻም
ለተቋማት የሚሰጥ ወቅታዊ የቅድመ መከላከል ስራ መስራትቀላልና ከባድ የመጠጥ ውሃ ብልሽት ጥገና ማከናወንየመጠጥ ውሃ ተቋማት መረጃ መሰብሰብ ማዘመንና መተንተን
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 