Skip to main content

የውሀ ሀብት ጥናትና ዲዛይን አስ/ ዘርፍ

የውሀ ሀብት  አስተዳደር ዘርፍ

ተግባርና ኃላፊነት

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብትን በማልማት፣ በመጠቀምና በማስተዳደር ለክልሉ ህዝብ ጥራቱን የጠበቀ፣ በቂና አስተማማኝ የሆነ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት አግኝቶ ጤንነቱ የተጠበቀና አምራች ዜጋ እንዲሆን፣የውሃ ሀብቱን በአግባቡ ተጠቅሞ ምርቱን እንዲያሳድግና ለክልሉ ሆነ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚው እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተወግደው ማየት እንዲቻል የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ወሳኝና ትልቅ ድርሻና ሚና እንደሚጫወት የሚታመን ስለሆነ በየደረጃው መሠረታዊ የጥናትና ዲዛይን ስታንደርድ በጠበቀ መልኩ በራስ ኃይል፣ በአማካሪ እና በመንግታዊ ባልሆኑ ድርጅት በማጥናትና በማስጠናት ችግር ፈቺ የሆነ ጥናትና ዲዛይን ዶክመንት በማዘጋጀት ሼልፍ በማድረግ ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ የማድረግ ሥራ መስራት ነው፡፡

በሌላ በኩል ዘርፉ በክልላችን የሚጠኑ ማናቸውም የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ዶክመንት ሰነድ በበላይነት የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ሲሆን በታችኛው መዋቅርም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተጠንተው የሚቀርቡ የጥናትና ዲዛይን ዶክመንቶች እንደየጥናት ይዘታቸውና መጠን አነስተኛ የሆኑ ተቋማትን በዞን ደረጃ ይሁንታ(Appraisals) በመስጠት የሚመራ ስሆን ከፍተኛ የሆኑ ተቋማት ጥናትና ዲዛይን በዘርፉ ይሁንታ(Appraisals) እየተሰጣ እንደሚመራ በBPR እና BSC ሰነድ ላይ የተመላከተ ነጥቦች ናቸው፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ ማናቸውም የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ዶክመንት በጥናትና ዲዛይን ደረጃ የተቋማት ዓይነትና ይዘት ታሳቢ ባደረገ መልክ ይሁንታ(Appraisals) ሳይሰጥ እና ዘርፉ ሳያፀድቅ ወደ ግንባታ ሂደት መግባት እንደሌለበት የጥናቱ ሰነድ ያረጋግጣል፡፡ 

በዘርፉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

የመጠጥ ውሃ ተቋማት አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን ስታንዳርድ ማኑዋል በማዘጋጀት ማሰራጨት፤

በጥራት የሚዘጋጅ አዳዲስ ዝርዝር የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የጥናት ስራዎች ሰነድ በማጥናት ተደራሸ ማድረግ፤

በጥራት የሚዘጋጅ ነባር ዝርዝር የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የዲዛይን ስራዎች ሰነድ በማዘጋጀት የማቅረብ፤

ዝርዝር የከተሞችና የገጠር መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች ከአማካሪዎች ጋር ዉል የመግባት አገልግሎት፣

የሙያ / የቴክኒክ አገልግሎት ድጋፍ የማድረግ፣

ተቋማት በዲዛይናቸዉ መሰረት ስለመሰራታቸዉ ክትትል የማድረግ አገልግሎት፤

አገልግሎት ለማይሰጡ  የመጠጥ ዉሃ ተቋማት የማሻሻያ ጥናት በማዘጋጀት የማቅረብ፣ 

የጥናትና ዲዛይን ዶክሜንቶች  ላይ ሙያዊ ግምገማ (Appraisal) በማድረግ ማቅረብ

የዲዛይን ለውጥ ሲኖር የዲዛይን ክለሳ ስራ የመስራት አገልግሎት፤

የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ስራ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መለየት፣ማጥናት፣የአገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን የመንደፍ አገልግሎት

በመያድ የሚከናወኑ የመጠጥ ውሀ ተቋማት ጥናትና ዲዛይን ስራዎች የመደገፍና  የመገምገም አገልግሎት ፣ይሁንታ(Appraisal) መስጠት ፣

በክልል፣ በዞንና በልዩ ወረዳ ሙያተኞች፤ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚዘጋጁ የሲቭል ወርክ ሥራዎች(Detail Engineering Study and Design, Drawing Albums) ከፍተኛና መካከለኛ የንፁህ መጠጥ ውሀ የጥናትና ዲዛይን ዶክመንቶችን በዴስክና በመስክ በመገምገም የአፕሬዛል ስራዎችን (ይሁንታ(Appraisal)) ያከናውናል፤ ማስተካከያዎችን አካቶ የጥናትና ዲዛይኑን ዶክመንት፤የስራ ዝርዝር /ስፔሲፊኬሽንና (Specifications) ቢኦኪው (BOQ)  ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤

የሥልጠና፣የምክርና የቴክኒክ አገልግሎት ፤

ዘርፉ በብቸኝነት ወይም በተሻለ ሁኔታ የሚያከናውናቸው በመሆናቸው ለሌሎች ተላልፈው የማይሰጡ ስራዎች ምንድናቸው? 

የመጠጥ ዉሃ ጥናትና ዲዛይን/አፕሬይዛል( Appraisal) (ይሁንታ አሰጣጥ)

  አዲስና ነባር የመጠጥ ዉሃ ጥናትና ዲዛይን  ስራዎች፤

የመጠጥ ዉሃ የማሻሻያ ጥናትና ዲዛይን ስራዎች 

የመጠጥ ዉሃ ጥናትና ዲዛይን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች 

ተቋማት በዲዛይናቸዉ መሰረት ስለመሰራታቸዉ ክትትል ማድረግ

ስታንዳርዶችን ማዘጋጀትና በስራ ላይ እንዲዉሉ ማድረግ