ራዕይ ተልዕኮና እሴት
አላማ
በክልሉ ያለውን ዕምቅ የገጸ-ምድርና የከርሰ ምድር የውኃ ሃብት በመለየት፤ የመስኖ ልማት አውታሮችን በማስገንባትና የተለያዮ አማራጭ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለመስኖ አመቺ በሆኑ አካባቢዎች የመስኖ ልማትን በማስፋፋት፤የገበያ ሰብሎችን እንዲያመርቱ በማገዝና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተጠቃሚዎችን ኑሮ ማሻሻል ነው፡፡
ራዕይ
የክልሉ አርሶ አደሮች ከዝናብ ጥገኝነት ተላቀው በዘመናዊ የመስኖ አመራረት ዘይቤ ላይ በመመርኮዝ ለገበያ የሚያመርቱ ዘመናዊ አምራቾች ሆነው መሰረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶና ኑሯቸው ተሻሽሎ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ
ከመንግስት፤ ከዕርዳታና ከብድር የሚገኝ ገንዘብ የዝናብ ዕጥረትና የስርጭት መዛባት ለሚከሰትባቸው እና ለመስኖ ፖቴንሻል በሆኑ አካባቢዎች በቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ሀይል በመታገዝ እና ተጠቃሚውን ህብረተሰብ በማሳተፍ በጥናትና በዲዛይን፤ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በመስራትና የመስኖ መሰረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት እንዲሁም የተገነቡ የመስኖ ተቋማት ዘለቄታዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግና በማስተዳደር ተጠቃሚው ህብረተሰብ በዓመት ቢያንስ ሁለቴና ከዚያ በላይ እንዲያመርት ማስቻል ነው፡፡
የኤጀንሲውእሴቶች
ውሀ ለግብርና ልማት
ለተጠቃሚው በቂና ዘላቂ የመስኖ ውሀ አቅርቦት
ጥራቱን የጠበቀና ወቅታዊ መረጃ መያዝ
ፍትሀዊ የመስኖ ተቋማት ስርጭት ማረጋገጥ
የህብረተሰብ ተሳትፎን በመስኖ ልማት ማረጋገጥ
ፍጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት
ህብረተሰቡን በታማኝነትና በግልጸኝነት ማገልገል
አዳዲስና ዘመናዊ የአሰራር ልምዶችን ማዳበር
ለሰራተኛው ተስማሚ የሆነ የስራ አካባቢን መፍጠር
ቅንጅታዊ አሰራርን ማዳበር
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 