የውሀ ሀብት /አስ/ዘርፍ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ስር ከተቋቋመ ዘርፎች ውስጥ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ አንዱና ሲሆን በዘርፉ በዋናነት የሚከናወኑ ተግባራት፡-
የውሃ ሀብት ብክለት ሁኔታ የሚያሳይ ጥናት እንዲሰራ ያደርጋል ፤የውሃ ሀብት ስርጭትና ክምችት የሚያሳይ በካርታ የተደገፈ መረጃ ያደራጃል፤የውሃ ሀብቱን አጠቃቀም ሽፋን (utilization coverage) የሚያሳይ መረጃ መስራትና ማስራጨት፤ውሃ ሀብቱን ማጥናትና ማስተዋወቅ ፤ውሃ ሀብቱን ማጥናትና ማስተዳደር፤ የውሃ ጥራት ግኝት መፍትሄ እንዲሰጥ ያደርጋል ፤የውሃ ፈቃድ (መጠቀም፤ የውኃ ነክ ስራዎች ሙያ ፈቃድ፤ የውሃ ስራ ግንባታ ፈቃድ፤የጉድጓድ ቁፋሮ፣የማማከር ፈቃድ፣ ቆሻሻ ውሃ ወደ ውሃ አካል የመልቀቅ ፈቃድ) እንዲሰጥ በማድረግ የቴክኒክ ድጋፍና ስልጠና መስጠት፣ አነስተኛ የውኃ ግንባታ ባለሙያዎች የሚሰጥ ግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል ፤ህገ-ወጥ የውሃ አጠቃቀም በተመለከተ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፣የውሃ ሀብት ስርጭት፤ክምችትና ጥራት መረጃ ያቀርባል፣የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ያቀርባል፣የውሃ ሀብት፤ፖሊሲና ስትራቴጂ ማስተዋወቅና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል፣የውሃ ጥራት ምርመራ እንዲደረግ ያደርጋል፣የቴክኒክ ድጋፍ፤ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ይሰራል፣በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሃ ሀብት አጠቃቀም እንዲኖር ማስቻል፣በአጠቃላይ ዘርፉ የውሃ ሀብት ክፍፍልና ምደባ በመስራት ፍትሃዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀም እንዲኖር የሚያደርግ ሲሆን እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውን በርካታ ባለሙያዎችን በስሩ የያዘ የውሃ ሀብት ጥናትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተደራጅቷል፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 