Skip to main content

የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባር

                                                  የኤጀንሲው  ሥልጣንና  ተግባር

በክልሉ  የአነስተኛ፤ መካከለኛና ከፍተኛ የመስኖ ልማት ተቋማት ለማስፋፋት የመስኖ አለኝታ /Potential/ ጥናት፤የዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ስራዎችን በራስ ሀይልና በአማካሪዎች ያስጠናል፣የወንዞች ፍሰት አቅጣጫ መግራት እና የጐርፍ መከላከያ ሥራዎች ጥናት ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎችን በራስ ሀይልና በአማካሪዎች ያከናውናል፣በክልሉ ለመስኖ ግንባታ ስራ የዉል ስምምነት ከተቋራጮች ጋር በመፈጸም ግንባታዉ እንዲካሄድ ያደርጋል፤የግንባታዉን ሂደትና የጥራት ደረጃ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ይቆጣጠራል፤ የክፍያ ሰነዶችን ያጸድቃል፤ክፍያ ይፈጽማል፤ግንባታቸዉ የተጠናቀቁ የመስኖ ልማት አዉታሮችን ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ያስረክባል፤የኮንትራት አስተዳደር ስራዎች ያከናዉናልጥገናና መልሶ ግንባታ ለሚያስፈልጋቸው ነባር የመስኖ ተቋማት አስፈላጊውን ጥገናና የመልሶ ግንባታ ስራ ያከናውናል፤

በክልሉ የመስኖ ልማትና የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን የማስፋፋት፤የማሰራጨትና የማስረፅ ስራዎችን ይሰራል፤

የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ማህበራትን ያደራጃል፣ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ ያደረጋል፣የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ተጠቃሚ ማህበራት የመስኖ አውታሩን እንዲከባከቡ ፣ እንዲያስተዳደሩ እና ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም አንዲሰፍን ክትትል ያደርጋል፣

በክልሉ በተለያዩ የመስኖ ልማት ስራ ላይ ለተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ  የግል ድርጅቶች ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤

የኢንቨስትመንት ወጪን ለመመለስ የሚያስችል ሚዛናዊና ምርታማ የሆነ የመስኖ መሰረተ ልማቶችን ግንባታ እንዲሁም እንክብካቤ አስመልክቶ ህብረተሰቡን ይቀሰቅሳል፤ስልጠና ይሠጣል፤