በቢሮውና በተጠሪ ተቋም በቀጣይ ጊዜያት በትኩረት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተካሄደ ።
መስከረም 26/2018 (ወልቂጤ)
በክልሉ ወሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ እና በማዕድንና ኢነርጂ ባለስልጣን በቀጣይ ጊዜያት ውስጥ በትኩረት የሚፈፀሙ ተግባራትን ላይ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ ፣ የቢሮው ምክትል ሃላፊዎች፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ የተጠሪ ተቋም የስራ ሃላፊ እንዲሁም የሚመለከታቸው በተገኙበት ውይይት ተካሄዷል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ እንደተናገሩት በንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ በቀጣይ ጊዜያት በ100 ቀናት ውስጥ የሚከናወኑ ስራዎችን ለማሳካት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ባስቀመጡት አቅጣጫና የትኩረት መስክ መሰረት በቀጣይ ጊዜያት በ100 ቀናት የሚተገበሩ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎችና የዘርፍ ተወካዮች ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀዋል።
እቅዱን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በክልሉ መንግስት አማካይነት በቀጣይነት የሚወርዱ አሰራሮችን ተከትሎ ቢሮው የደረጃው በሚገኙ አደረጃጀቶች ተገቢውን በመፈፀም በድጋፋዊ ክትትል እንደሚያጠናክር የተናገሩት አቶ ማቴዎስ በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሙያዎችና ሌሎችም የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በውይይቱ የተገኙ የስራ ሃላፊዎች የ100 ቀናት እቅዱ የተጀመሩ ሥራዎችን ከማጠናከር ባሻገር በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንደሚያፋጥን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ለምቦሶ እና የቀድሞ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዳዊት ኃይሉ እንዲሁም የቢሮው ምክትል ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው በተገኙበት በቢሮው የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በየዘርፉ በሚገኙ የስራ ክፍሎች ባሉ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ለአዲሱ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 