በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በአውድ ቀበሌ የተገነባ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት ክፍት ተደረገ።
መስከረም 15/2019 (ወልቂጤ)
በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በአውድ ቀበሌ በሰርሊና በጎ አድራጎት ድርጅት ከ5.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 19 የምንጭ እና የጉድጓድ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ተገለጸ።
የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሰበ ካብቱ የሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ዉሀ እጥረትን በመቅረፍ ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ እንዲኖር አመርቂ ተግባር በመፈፀሙ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት በወረዳዉ በአውድ ቀበሌ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ሠዎች ውሀ በቀላሉ ሳይንገላቱ እንዲያገኙ ያደረገበት መንገድ አበረታች መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋማትን በአግባቡ በጥንቃቄ እንዲጠብቁት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
የሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት አስተባባሪ የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ እንደገለፁት ዉሀ ለሰዉ ልጆች መሠረታዊ ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዉ ሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት አቅመ ደካማ እናቶች እና ወገኖች እንዲያገኙ ማድረግ የአእምሮ እርካታ ይሰጣል ብለዋል።
በወረዳው የአውድ ቀበሌ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎትን በቅርበት ማግኘት በመቻላቸው ደስታቸውን ገልጸዋል ሲል ከወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 