በብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቆሼ ከተማ የጥልቅ መጠጥ ውሃ ተቋም ተጠግኖ ለአገልግሎት መብቃቱ ተገለፀ።
መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)
በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ከተማ ነዋሪዎችን ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ፍላጎት ለመቅረፍ የተገነባው የጀይካ (JICA) ጥልቅ መጠጥ ውሃ ተቋም በኤሌክትሮ ሜካኒካል አካላት ብልሽት ምክንያት ላለፉት ሶስት ወራት ከአገልግሎት ውጭ በመሆኑ የጥገና ስራ በማካሄድ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን የልዩ ወረዳው ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ከልዩ ወረዳው መንግስት እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኘው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጉድጓዱ የኤሌክትሮ ሜካኒካል አካል ( አዲስ ፓምፕ ከነሞተሩ አዲስ ዘመናዊ ስዊች ቦርድ እና አዲስ የኤሌክትሪክ ኬብል ሙሉ በሙሉ በአዲስ እንዲቀየር ተደርጎ ተቋሙ ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የልዩ ወረዳ ው ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ባንዳ ገልፀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ፣ የልዩ ወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት እና የልዩ ወረዳው ባለሀብቶች የውሃ ተቋሙ ተጠግኖ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አቶ ዘካሪያስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የቆሼ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ደበሮ በበኩላቸው የጀይካ ጥልቅ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ የከተማው ዋና የውሃ ምንጭ በመሆኑ የጉድጓዱ የኤሌክትሮ ሜካኒካል አካል ሙሉ በሙሉ በአዲስ መተካቱ ገልፀው ጥገናው በጥራትና በተሟላ ሁኔታ እንዲከናወን የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በድጋሚ አቅርበዋል።
የዉሃ ተቋሙ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር በትዕግስት ለጠበቀው የከተማው ነዋሪዎች ምስጋናቸውን የገለፁት አቶ ግርማ የውሃ ተቋሙ በቀጣይነት ዘለቄታዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከልዩ ወረዳው ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 