የክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና የዘርፍ ኃላፊዎች ከዳይሬክቶሬቶች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የስራ ግብ ስምምነት ተፈራረሙ።
ነሃሴ 12/2018 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ቀደም ሲል ከተጠሪ ተቋማትና ከቢሮው ምክትል የስራ ሃላፊዎች ጋር ያካሄደውን የግብ ስምምነት ፊርማ ተከትሎ የቢሮው ምክትልና የዘርፍ ሃላፊዎች ከስራቸው ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የስራ ግብ ስምምነት ፊርማ ስነስርአት አካሄዋል።
በስነ-ስርዓቱ በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ ሮ አለይካ ሽኩር ከውሃ ሀብት ጥናትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከድር ታምሬ ፣
የቢሮው ምክትል ሃላፊና የመጠጥ ውሃ ሀብት ጥናትና ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አየለ ኬርጋ (ኢ/ር) ከመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ አቢዮ
እንዲሁም የቢሮው ምክትልና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙላቱ ጡሞሮ ከመጠጥ ውሃ ግንባታ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገረመው አቡና እና ከመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶት ዳይሬክተር አቶ ኡስማን በድሩ ጋር የ2019 በጀት ዓመት የስራ ግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በእለቱ የግብ ስምምነት ሰነድ ከመፈራረም ባሻገር በየዘርፉ ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር በግብ ስምምነቱ ሰነድ አተገባበር ላይ በየደረጃው ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተደርሷል።
ከየዘርፉ የሚገኙ ሰራተኞች ለስምምነቱ ውጤታማነት በቁርጠኝነት የሚንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጨረሻም በየዘርፉ የሚገኙ ዳይሬክተሮች በስሮቻቸው ከሚገኙ የቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 