የቢሮውና የተጠሪ ተቋማት ዕቅድ ግብ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሄደ!
ነሃሴ 07/2018 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ከተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ከቢሮው ምክትል የዘርፍ ሃላፊዎች ጋር በ2019 የበጀት ዓመት ስራዎች የግብ ስምምነት ተፈራርሙ።
የግብ ስምምነቱን የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ከክልሉ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር)፣ ከማዕድንና ኢነርጂ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን መኔዶ፣ በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ ከክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ ሮ አለይካ ሽኩር ፣ ከቢሮው ምክትልና የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አየለ ኬርጋ (ኢ/ር) እና ከቢሮው ምክትል እና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳኒቴሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሙላቱ ጡሞሮ ጋር የግብ ስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በግብ ስምምነቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእዕት በቢሮውና በተጠሪ ተቋማት አማካይነት የሚከናወኑ ተግባራትን ካለፉት አመታት በተለየ መልኩ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ እንደሚፈፀም ገልፀው በአመራሩ የሚመራ ኮማንድ ፖስት በማዋቀር የተጠናከረ ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 