Skip to main content

የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ በየም ዞን ደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ አሮጌ መኖሪያ ቤት በማፍረስ አዲስ ቤት ግንባታ አስጀምሩ።

ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም(ወልቂጤ)

የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቢሮው የስራ ሃላፊዎች ፣ ማናጅመንት አባላት ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሃይሉ እንደገለጹት ሃገር እየመከረች ባለችበት ወቅት መሰል የበጎ ተግባራት ላይ መሳተፍ መርሃ ግብሩን ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

‎በጎነት ሀገርና ሕዝብ በዜጎች አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣ ነባሩን የአብሮነት እና የመደጋገፍ ባሕላችንን የምናድስበት በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ጠቁመዋል።

‎ለሚከናወነው የቤት ግንባታ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሲሆን ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል።

‎የደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሴ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፊበት ወቅት እንዳሉት አቅመ ደካማ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍልን ቤት ለመገንባት እና ከነበረው ችግር እንዲላቁ ላደረጉ የክልሉ የውሃ ቢሮ የስራ ሃላፊወዎችና የማኔጅመንት አካላትን አመስግነዋል።

‎የቤቱ ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸው ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳሰበዋል።

‎የቢሮው ምክትል ሃላፊና የመጠጥ ውሃ ሃብት ጥናት ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አየለ ኬርጋ (ኢ/ር) በበኩላቸው የበጎ ተግባር የሰው ልጆች አብሮነታቸውን የሚያጸኑበትና የመደጋገፍ መስተጋብር የሚጎለብትበት አንዱ ተግባር መሆኑ በዚህ ዓይነት መልካም ነገር ላይ መሳተፍ ጥቅሙ እጥፍ ድርብ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ቢሮው የተቋቋመበት አላማም ማህበራዊ አገልግሎት ተደራሽ የማድረግና የህዝብ ተጠቀሚነትን ማረጋገጥ በመሆኑ መሰል የበጎ ስራዎች በሌሎችም ቦታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

‎በእለቱ የቤት ግንባታ የሚደረግላቸው የደሪ ሳጃ ዙሪያ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት ቤቱ ለመኖር ምቹ ባለመሆኑ ይቸገሩ እንደነበር አንስተው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Image