የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል- የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
(ሐምሌ 11/2018)
የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
ቋሚ ኮሚቴው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መርሃ ግብር የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ዕቅድ ክንውንን በመገምገም አጠናቋል።
የቢሮውና ተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴውም ሪፖርቱን አድምጦ የቃል ግብረ መልስ ሰጥቷል።
የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ልክነሽ ስርገማ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ ሴክተሩ ባለው ውስን ሀብት በንፁህ መጠጥ ውሃ፣ በመስኖና በማዕድን ልማት ስራዎች ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል።
የክልሉ መንግስት በክልል ማዕከል ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ
አቅጣጫ ማስቀመጡን ያስታወሱት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ፣ በዚህ ረገድ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት አሁንም አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተደራሽነቱን ለማሻሻል በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
በማዕድን ልማት ስራ ላይ ገቢን በተገቢው መሰብሰብና ማዕድንን መልሶ ማልማት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ወይዘሮ ልክነሽ፣ በመስኖ ተቋማት አስተዳደር ላይም በትኩረት በመስራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ጨምሮ የተጠሪ ተቋማቱ የስራ ሃላፊዎች ፣ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 