በውሀ ጥራት ቁጥጥር ፣በተቋማት አስተዳደርና በውሀ አጠቃቀም ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚንቀሳቀሱ ሰልጣኞች ተናገሩ ።
ግንቦት 16/2018 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሀላባ ዞን በ2018 HUMAN CAPITAL OPERATION (HCO) ፕሮግራም ላይ ለታቀፉ ወረዳዎች በውሀ ጥራት ቁጥጥር እና ተቋማት አስተዳደርና በውሀ አጠቃቀም የአሰራር ስርዓት ላይ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና አጠናቋል ።
በውሀ ጥራት ቁጥጥር ፣በተቋማት አስተዳደርና በውሀ አጠቃቀም ላይ በስልጠና መድረኩ ያገኙትን እውቀት ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የስልጠና ተሳታፊዎች ተናግረዋል ።
የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የዕቅድ፣ በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም ቀድሩ በስልጠና መድረኩ ማጠቃለያ (HCO) ፕሮግራም በሰው ልጅ አእምሮ እድገት ላይ አተኩሮ የሚሰራ በመሆኑ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ፕሮግራሙን በተገቢው መደገፍና እስከ ታችኛው መዋቅር ማውረድ ይገባል ብለዋል ።
የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የተበላሹ የመጠጥ ውሃ ተቋማትን በወቅቱ መጠገን እንደሚገባ ጠቁመው የህብረተሰቡን አቅም በመጠቀም የሀይል አቅርቦት ላይ የገጠሙ ችግሮችን በታዳሽ ሀይል እንዲተኩና በፕሮግራሙ ተጨማሪ እድሎችን ለማግኘት በየደረጃው የሚገኙ አካላት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ስዩም ተናግረዋል ።
በቢሮው የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኡስማን በድሩ በበኩላቸው የመጠጥ ውሀ ተቋማት አስተዳደርና የውሀ አጠቃቀም መመሪያን በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልጸው ወቅቱን የጠበቀና የዘመነ መረጃ ልውውጥ በየደረጃው ሊተገበር ይገባል ብለዋል ።
በየውሀ ሀብት ጥናትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውሀ ጥራት ባለሙያ ወ/ት የውብዳር ተስፋዬ እንደገለጹት የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በውሀ ጥራት ቁጥጥር ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሳለጥ የላብራቶሪ መሳሪያዎችን በማሟላት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ስር መዋቅሮችም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተናግረዋል ።
ከሰልጣኞች መካከል በሀላባ ዞን ውሀ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ የመጠጥ ውኃ ተቋማት ጥገና አስተዳደር የስራ ቡድን መሪ አቶ መንሱር አባኮ የመጠጥ ውሀ የጥራት ችግር ምክንያቶችን ከመለየት ባሻገር በውሀ ህክምና መንገዶች እና ተሻሽሎ በወጣው የውሀ ተቋማት አስተዳደርና የውሀ አጠቃቀም መመሪያ ላይ የተሻለ እውቀት ማኘታቸውን ገልፀው ።
በዞኑ የአቶቴ ኢሎ ወረዳ ውሀ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሳራ ቡጃማ በውሀ ጥራት አጠባበቅና በተቋማት አስተዳደር ዙሪያ ቀጣይ ተግባራትን ለማሳለጥ ከስልጠና መድረኩ ሰፊ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል ።
ስልጠናው በፕሮግራሙ ለታቀፉ በሀላባ ዞን የዞን ማዕከል፣ አቶቴ ኢሎ ወረዳ እና ዌራ ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 