ህዝባችንን የመልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ የመስጠቱን ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን :- የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ
በቀቤና ልዩ ወረዳ በዳይሬክት ኤይድ (Direct Aid) ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት ከ18 ሚሊየን ብር ወጪ በላይ የተገነባው የሱንካ - ጎራሰዴ የጥልቅ ውሃ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።
(ወልቂጤ ግንቦት፣ 03/2018 ዓ.ም)
የቀቤና ልዩ ወረዳ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሚን በደዊ በምረቃው ፕሮግራም እንደተናገሩት የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ለዜጎች የረዥም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልፀው ብልፅግና ፓርቲ የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ እየሰጠ ነው ብለዋል።
አክለውም ብልፅግና ፓርቲ በገባው ቃል የሚያከብር ፤ ያቀደውን የሚፈፅም፤ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ ነው መሆኑን በመግለፅ ሌሎች የሚቀሩ የልማት ስራዎችን ለመጀመር የተጀመሩትንም ለማጠናቀቅ ሁሉንም አቀፍ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል ።
በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር እንደተናገሩት የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር ውሃ አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ፓርቲያችንና መንግስታችን የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠርና አጋር አካላት በማስተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል ።
የዳይሬክት ኤይድ ድርጅት ማናጀር አቶ ጦሃ እንደተናገሩት ድርጅታቸው በሌሎች ቦታዎችም እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ይህ የውሃ ፕሮጀክት በጥራትም በአቅምም ከፍ ያለ በመሆኑ በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባል ብለዋል።
አክለውም 24 የሶላር ፓኔል ያለውና አንዱ ከ 500 በላይ ዋት የሚያመነጭና 7 ሜትር ፐ/ሰከንድ የመግፋት አቅም ያለው መሆኑንና ስለ አጠቃቀሙ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ስልጠና የተሰጠ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ በየጊዜው ጥናትና ክትትል በማድረግ ያለበትን ደረጃ የማሻሻልና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የማስፋፋት ስራ የሚሰራ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ልዩ ወረዳ ውሃ፣ መአድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጁሃር ጀማል እንደገለፁት ውሃ የሁሉ ነገር መሰረት በመሆኑ የህፃናት ጉልበት ከመበዝበዝ ፣ የእናቶችና የሴቶችን ድካም ለመቀነስ አይነተኛ ሚና ያለው ነው ብለዋል።
ይህም የሁለቱ ቀበሌ ውሃ ችግር የሚቀርፍ መሆኑን በመግለፅ ሁለቱንም ቀበሌ ሙሉ ለሙሉ ማስጠቀም የሚችል በመሆኑ የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል።
በምረቃው ፕሮግራም የፌዴራል ፣ የክልል፣ የልዩ ወረዳውና የወልቂጤ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የወልቂጤ ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ እጩዎች፣ እና የቀበሌው የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ።
የልዩ ወረዳው መንግስት ኮምኒኬሽን ዘግቧል
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 