የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በንፁህ መጠጥ ውኃ እና በመስኖ ልማት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጀምሮ በባለፉት 2 ዓመት ከዘጠኝ ወራት ውስጥ በክልላችን በመንግስት፣ በአጋር አካላትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ 283 የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታቸው ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በንፁህ መጠጥ ውኃ እና በመስኖ አውታር ግንባታና ልማት ዘርፎች በርካታ አመርቂ ስራዎች በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
በንፁህ መጠጥ ውሀ ዘርፍ በ2016 የበጀት ዓመት የቡ-ሄጎ፣ የቂንቂቾ እና የዋጮ ዳንቃ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በገጠርና በከተማ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተገነባውን ጨምሮ 56 የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶን በማጠናቀቅ 215,109 ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በ2017 በጀት ዓመት የውሀ አቅርቦቱን ለሁሉም ለማድረስ በተደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በከተሞች የቡኢ፣ የሺንሺቾ እና የዳሎቻ መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንዲሁም በገጠር የቢላሎ እና የመቆርቆር በአጠቃላይ በግብረ ሰናይ የተገነቡትን ጨምሮ 120 የመጠጥ ውኃ ተቋሟትን በማጠናቀቅ 279,811 የህብረተሰብ ክፍሎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ በክልሉ መንግስት በተሰጠው ልዩ ትኩረት የሶዲቾ፣ ቁልቢ፣ ሰሜን ቆሼ በGCF ፕሮግራም ወንጀላ፣ ኦሞጮራ፣ አምቢቹ ጎዴ በSDG ፕሮግራም ዌይራ ገረድ፣ ዱግዳ ጎሮ በዋን ዋሽ ሳንኩራ ብዝሀ መንደር በCR WaSH ፕሮግራም፣ 1ኛ ጤፎ በሆርን ኦፍ አፍሪካ እና ሌሎች ጨምሮ በአጠቃላይ 107 የመጠጥ ውኃ ተቋማት ግንባታን በማጠናቀቅ 436,148 ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወራት በፌደራል፣ በክልሉ በመንግስት፣ በአጋር አካላትና በህብረተሰቡ 283 የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታቸው ተጠናቆ ለ931,068 ህብረተሰብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በመስኖ ተቋማት ልማት የክልሉ መንግስት ምስረታ ተከትሎ ባለፉት ሁለት አመት ከዘጠኝ ወራት የሀንዴሻ፣ አጃቾ፣ ወልዲያ፣ ሬቡ ፣ ሀኦ ፣ ሲምቢጣ 2፣ ኤደነባ፣ ሳቶራ ጨምሮ በአጠቃላይ 14 የመስኖ ተቋማት ግንባታን በማጠናቀቅ 2027 ሄክታር መሬት በማልማት 5497 አባወራና እማወራ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በክልሉ ለረዥም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆን የተጓተቱና የሰነበቱ ፕሮጀክቶች በነባሩ ክልል ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመጠጥ ውኃ እና የመስኖ ተቋማት ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራት በመመራታቸው ለተግባር ውጤታማነትና ለተገኘው ስኬት ዋነኛ መገለጫ ናቸው። በያዝነው በጀት አመት ቀሪ ወራት ውስጥ በርካታ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለምረቃ እንደሚበቁ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 