በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ በዋን ዋሽ 1 እና 2 ፕሮግራም ከ 22.7 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰራው የገባባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ!
ሚያዚያ 24/2018 (ወልቂጤ)
በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ በዋን ዋሽ 1 እና 2 ፕሮግራም ከ 22.7 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰራው የገባባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኡስማን ሱሩር መንግስት በሀገር ደረጃ አዳዲስ ስልቶችን ነድፎ ለህዝብ ተጠቃሚነት መጠነ ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በዋናነትም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በኩል በልዩ ትኩረት ተሰርቶ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ቢሮ ሀላፊው አስታውሰዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ባስተላለፉት መልዕክት የዞኑ መንግስት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ለማሟላትና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በልዩ ሁኔታ ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።
የንጹህ መጠጥ ውሃን ተደራሽ ለማድረግ በተሰራው ስራ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ከ2 መቶ ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍልን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
በቅርብ ዓመታት በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የገለጹት አቶ ዘይኔ ለረዥም ጊዜ ሲጓተት የቆየው የአንጀሌ የውሃ ፕሮጀክት በተያዘው አመት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አስረድተዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር፣ የስልጤ ዞን አስተባባሪ አካላት እና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የወረዳው የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 