Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

እንኳን ለ1ሺ 447ኛዉ ዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም

አደረሳችሁ! አደረሰን!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፦ እንኳን ለ1ሺ 447ኛዉ ዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ።

በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በልዩ ልዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ታጅቦ የሰነበተዉ ታላቁ የረመዳን ወር ማሳረጊያዉን የሚያገኝበት የዒድ አልፈጥር በዓል እነሆ ደረሰ!፤ ዒድ ሙባረክ!

ታላቁ የረመዳን ወር በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ለፈጣሪ (ለአሏህ ) ትዕዛዛት የመገዛት፣መልካም ተግባራትን የማብዛትና ከተከለከሉ ጉዳዮች የመራቅ ትጋት የሚበረታበት ነዉ፤ ወሩ የይቅርታ፣ የመተባበር፣ የንሰሃና የፀሎት ወቅትም ነዉ።

በመሆኑም፣ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳኑ ወር ሲያዘወትራቸዉ የቆዩ የአብሮነት፣ የመደጋገፍ፣ የመጠያየቅና መተባባር እሴቶችንና ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል።

ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንድም እና እህት ህዝቦች ጋር በመሆን በዘላቂ ሠላም ግንባታ፣ በስነ ምግባር የታነፀ ሀገር ወዳድና ምክንያታዊ ወጣት በመገንባቱ ሂደት፣ በአጠቃላይ በሀገር ግንባታው ሂደት አስተዋጽኦውን አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ ።

በዓሉ የደስታ፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ ፣

ዒድ ሙባረክ!

አመሠግናለሁ !

Image