Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በከምባታ ዞን ከ208 ሚሊየን በላይ ብር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች መርቀው ስራ አስጀመሩ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) በከምባታ ዞን ግንባታቸው የተጠናቁ የመንገድ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በዛሬው እለት የተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶቹ ከ208  ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን ከ76 ሺ በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ያደርጋሉ።

የመስኖ ፕሮጀክቶቹ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና ያላቸው ሲሆን በዚህም 200ሄ/ር መሬት የማልማት አቅም አላቸው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር )ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት አውታሮችን መርቀው በከፈቱበት ጊዜ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል።

የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ ልምድ በማዳበር በሁሉም መስክ ውጤታማ ስራ ተግባራዊ እየተደረገ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የክልሉ መንግስት ያለውን ዝግጁነት ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

Image