በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎችና 1 ልዩ ወረዳ በኮዋሽ ፕሮግራም የተጀመሩ የውሀ ፣ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ስራዎች በተደራጀ መንገድ ሊመራ እንደሚገባ ተገለፀ ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በኮ-ዋሽ ፕሮግራም በአራተኛው ምዕራፍ
የባለፉት ሰባት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሂዷል ።
በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሃ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዉሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አላይካ ሽኩር በመድረኩ እንደገለጹት በክልሉ በንፁህ መጠጥ አቅርቦት ፣ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በክልሉ መንግስት ፣ በቢሮውና አቻ ተቋሟት ብርቱ ጥረት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመከናወን ላይ የሚገኘው ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል ።
በየወረዳዎቹ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በወቅቱና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት በማጠናቀቅ በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ለተጀመረው የኮ-ዋሽ ፕሮግራም ቀጣይነት እንዲኖረው በየደረጃው የሚገኙ የፊት አመራሮች የድርሻቸውን ሊወጡና ተግባሩ በተደራጀ መንገድ ሊመራ ይገባል ብለዋል ።
እያንዳንዱ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወረዳ/መዋቅር ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በልዩ እቅድ እስከ ግንቦት 30/2018 ለማጠናቀቅ መንቀሳቀስ እንደሚገባው አመላክተው ቢሮው የጀመረውን ድጋፋዊ ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አለይካ ገልፀዋል ።
በቢሮው የኮ-ዋሽ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብዮት ስኔቦ እንደገለፁት በኮዋሽ ፕሮግራም የሳኒቴሽንና ሀይጂን ፕሮጀክቶች ላይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ውጤታማት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በተያያዘም የፊዝካልና የፋይናንሻል አፈፃፀም ልዩነት የታየባቸው ወረዳዎች ከወዲሁ ተገቢው እርምት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል ።
ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በየወረዳው የሚገኙ የዋሽ ቲምና ቴክኔካል ኮሚቴ እንቅስቃሴ ማጠናከር ላይ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል ።
አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አሰተያየት በመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ፣ደረጃው የጠበቀ መጸዳጃ ቤት በመገንባት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት የተጀመረውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በየአካባቢው ያሉ ቀሪ ተግባራት በመድረኩ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት በአጭር ጊዜ ለመጨረስ በየደረጃው ያሉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመስራትና ከመድረኩና በድጋፋዊ ክትትሉ በተገኘው ግብአት መሰረት የጌታ ወረዳ የተቀናጀን አሰራር ልምድ ወስደው እንደሚተገብሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል ።
በመድረኩ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አየለ ኬርጋ ኢ/ር ፣ ከክልሉ ጤና ፣ት/ት ፣ ፋይናንስ ቢሮዎች የኮዋሽ ፎካሎች፣ ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና ሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 