በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ከ12 ሺ በላይ ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሙዳ ማያፋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጃክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ።
ጥር 4/2018 (ወልቂጤ)
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የሙዳ ማያፋ ቀበሌ ዲኖቆሳ ቀበሌን የሚያካትት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነእየሱስ ግብረሰናይ ድርጅት ፈንድ የተሰሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ማስፋፊያና ቁፋሮ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል ።
የማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል ውሃና መስኖ ቢሮ ሀላፊ ደዊት ሀይሉ እንደተናገሩት ዛሬ የተፈታው የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ብቻ ሳይሆን የትምህርት ችግር ነው የጤና ችግር ነው በማለት በውሃ ችግር ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ በውሃ ወለድ በሽታ ህፃናት እንደሚታመሙ ገልፀው ህብረተሰቡ ዛሬ የተመረቀውን ውሃ በጥንቃቄ ማያዝ እንደለበት አስገንዝበዋል ።
አቶ ደዊት አያይዘው እንደገለፁት ፕሮጅክቱ ልዩ የሚያደርገው በታዳሽ ሀይል የተገነባ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፃው የፕሮጀክቱን አስተባባሪዎችን እና ህብረተሰቡን አመስግነዋል ።
በምረቃው ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደተናገሩት የውሃን ችግር ሊፈቱ ቀንና ማታ ስለፉ የነበሩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችን እና ሌሎችንም ባለድርሻ አካለትን አመስግነዋል ።
ለምረቃ የበቃው የንፁህ መጣጥ ውሃ ፕሮጀክት ህብረተሰቡ እንዲጠብቅ መልዕክት ያስተላለፉ ስሆን በዝርጋታ በማስፋፊያ ስራዎች ፕሮጀክቱ በቀጣይ ድጋፍ ማድረግ እንደለበት አሳስበዋል ።
የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በበኩላቸው የአካባቢው ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍለጋ ረጅም መንገድ በመጓዝ የሚደርስባቸውን እንግልት በተለይ የእናቶችን ልፋት ከማስቀረት አኳያ ያለው ፋይዳ ቀላል የማይባል ነዉ ብሏል፡፡
በተለይ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ችግርን ለመቅረፍ መካና የሱስ ድርጅት እየሠራ ያለዉን ስራ አድንቀው ቅንጅታዊ ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል::
አቶ ከድር አያይዘው እንደተናገሩት የመካና የሱስ ድርጅት አስተባባሪዎችን በራሳቸው እና በወረዳው አስተዳደር ስም አመስግነዋል ።
የሀላባ ዞን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ሀላፍ አቶ አብዲ ከይራዲን ህብረተሰቡ የንፁህ መጣጥ ውሃ በሃላፊነት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል ።
የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቀው የንፁህ መጠጥ ውሃ ህብረተሰቡ በዘላቂነት እንዲጠቀም ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካለት ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ክትትል እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል ።
ፕሮጀክቱ 12,000 ህብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዉ ይህ ሁሉ ህብረተሰብ ለረዥም ዓመታት የነበረን ችግር ይቀርፋል በሚል የወረዳው መንግስት ኮምኒኬሽን ዘግቧል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 